Normal 0 false false false EN-US X-NONE X-NONE /* Style Definitions */ table.MsoNormalTable {mso-style-name:"Table Normal"; mso-tstyle-rowband-size:0; mso-tstyle-colband-size:0; mso-style-noshow:yes; mso-style-priority:99; mso-style-qformat:yes; mso-style-parent:""; mso-padding-alt:0in 5.4pt 0in 5.4pt; mso-para-margin-top:0in; mso-para-margin-right:0in; mso-para-margin-bottom:10.0pt; mso-para-margin-left:0in; line-height:115%; mso-pagination:widow-orphan; font-size:11.0pt; font-family:"Calibri","sans-serif"; mso-ascii-font-family:Calibri; mso-ascii-theme-font:minor-latin; mso-hansi-font-family:Calibri; mso-hansi-theme-font:minor-latin;}

ደብረ ማርቆስ የተመሰረተችው በደጃዝማች ተድላ ጓሉ የጎጃም ክፍለ ገዥ በነበሩበት ጊዜ ነው

ምስራቅ ጎጃም ዞን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ 11 ዞኖች መካከል አንዱ ሲሆን 16 የገጠር ወረዳዎች 4 የከተማ አስተዳደሮች የተከፋፈለ ነው፡፡

በሰሜን /ጎንደር በደቡብ ኦሮሚያ፣ በምስራቅ /ወሎና ሰሜን ሸዋ፣ እንዲሁም በምዕራብ ምዕራብ ጎጃም ያዋስኑታል፡፡

በዞኑ የሚኖረው የህ/ብዛት 2.3 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 89.08 በመቶ በገጠር የሚኖርና በግብርና ላይ የተሰማራ ሲሆን 10.92 በመቶው ደግሞ የከተማ ኗሪ ነው፡፡ 432 ቀበሌዎችን ያቀፈው ምስራቅ ጎጃም 1 ሚሊዮን 407 138 ሄክታር የመሬት ስፋት ሲኖረው ከጠቅላላው የክልሉ የቆዳ ስፋት 8.12 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናል፡፡

1 ሚሊዮን 407 138 ሄክታር የመሬት ስፋት ውስጥ 521840 ሄክታር ለኣመታዊ ሰብል፣ 91464 ሄክታር ለደንና ቁጥቋጦ፣ 165605 ሄክታር ለግጦሽ 23848.55 ሄክታር በውሃ አካል የተሸፈነና 6652500.4 ሄክታር ጥቅም የማይሰጥና ሌሎችን የያዘ ነው፡፡ ዞኑ ውርጭ 21 % ደጋ 11.9 % ወይና ደጋ 80.55% እና ቆላ 5.45 የአየር ንብረት ክፍሎች የተከፋፈለ ነው፡፡ የመሬት አቀማመጡም 7.8% ተራራማ 67.3% ሜዳማና 24.9% ሸለቋማ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ 800 አስከ 4200 ሜትር ከፍታ አለው፡፡ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም 1200 አስከ 1600 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ሲሆን 10 እስከ 13 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ የሚደርስ የሙቀት መጠንም አለው፡፡

በዞኑ ውስጥ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ ፣በቆሎ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ምስር፣ ሽምብራ፣ ማሽላ፣ የቅባት እህሎች፣ ወዘተ በስፋት የሚመረቱ ሲሆን የዳልጋ ከብት፣የጋማ ከብት በግና ፍየል፣ ዶሮና ሌሎችም በስፋት በስፋት ይረባሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓት በዞኑ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በመልካም አስተዳደራዊ ዘርፎች በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን ጥቂቶች ብቻ ለአብነት ያህል እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ግብርና

በዞኑ መልካዓ ምድር አቀማመጡና በአየር ንብረቱ ለገብርና ስራ በታም ተስማሚ በሆነ የተፈጥሮ ሀብት የታደለ፣ ለእንስሳት እረባታም ሆነ ለሰብል ልት ተመራጭነት ያለው ትረፋ አምራች ዞን ነው ፡፡ ለአብነት ያህል 2002/2003 የምርት ዘመን በመህር ሰብል ብቻ 580141ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ 21780926 ኩንታል ምርት የተገኘ ሲሆን 5488 ኩንታል ምርጥ ዘር 419131 ኩንታል ዳፕ ዮሪያ ማዳበሪያ ስራ ላይ ውሏል፡፡ ዞኑ በተለይ መጤፋ፣ በስንዴ፣ በበቆሎ፣በገብስና በጥራጥሬ የእህል ዓይነቶች የታወቀ ነው፡፡ በወተት ሀብትልማትና በማር ምርትም የሚታማ አይደለም፡፡

ዞን የተትረፈረፈ 70 ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ባለቤት በመሆኑ በመሆኑ የመስኖ ልማት ስራ አበረታች ነው፡፡

በዚህ ዓመትም በዞኑ ምርት ምርታማነት በእጥፍ ለማሳደግ በተያዘው እቅድ መሰረት አርሶ አደሩ በመኅር ሰብል በመስኖ ልማት በእንስሳት ሀብት ልማት በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ አስከ መንደር ድረስ ስልጠና ወስዶና 13722 የልማት ቡድን ተደራጅቶ ወደ ተግባር ስራ ተሰማርቷል፡፡ በሁሉም ቀበሌዎች ሶስት ሶስት የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኞች ተመድበው አርሶ አደሩን በቅረብ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ኢንቨስትመንት

ዞኑ ኢንቨስት ለሚደርጉ ባለሀብቶች የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት 24745783 ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 591 ባለሀብቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ማለትም በኢንዱስትሪ በግብርና በኮንስትራክሽን በማዕድን በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በንግድ ተሰማርተው 116997 ዜጎች የስራ አድል ተፈጥሯል፡፡ በቀጣይ በተለይ በገተር በሰብል ልማት በደን በእጣንና ሙጫ የስራ ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች 123128 ሄክታር ቦታ ተዘጋጅቶ በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡

ጥቃቅንና አነስተኛ

በዞኑ 33114 ወነወድና 20239 ሴት ስራ አጥ ወገኖች በተለያዩ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማለትም በእንጨትና ብረታብረት በሽመና፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴልና ቱሪዝም በግብርና በንግድ በእደ ጥበብ፣ በማዘጋጃ ቦታዊ አገልግሎት ወዘተ እንዲሰማሩ የተደረገ ሲሆን 48426990ያህል ካፒታል ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎች ድህነትን ተረት በማድረግ ራሳቸውን ከመርዳት አልፈው ቤተሰቦቻቸውን በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ፡፡ ወደ ባለሀብትነት የተሸጋገሩም አልጠፉም፡፡ ለዚህም ማሳያ 9 ግለሰቦችና ማህበራት ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ተሸጋግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በደ/ማርቆስ ከተማ የህ/ሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታትና የከተማውን ውበት ለመጠበቅ 539 ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች በመተላለፍ ላይ ሲሆኑ 961 ቤቶች ደግሞ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

ትምህርት

የህብረተሰቡን የትምህርት ጥማት ለማርካት በአሁኑ ሰዓት በዞናችን 332 አማራጭ 770 አንደኛ ደረጃ /ቤት 25 ሁለተኛ ደረጃና 14 መሰናዶ /ቤቶች በመንግስትና በህብረተሰቡ ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ 292620 ወንድና 290828 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ሲሆኑ በተለይ በአንደኛ ደረጃ /ቤት የሴቴ ተማሪዎች ተሳትፎ 10% በላይ ደረሷል፡፡

ትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ 12924 መምህራን ተቀጥረው እያገለገሉ ሲሆን በአንደኛ ደረጃ /ቤት የተማሪ መጽሀፍ ጥምርታ 1 1 የክፍል ተማሪ ጥምርታ 1 56 እና የመምህ ተማሪ ጥምርታ 1 50 ደርሷል፡፡

አጠቃላይ የት/ ሽፋኑ እንደ ዞን 95.72 ደርሷል፡፡ በሌላ በኩል አንድ ዩኒቨርሲቲ 9 የመንግስትና 12 የግል ኮሌጆች ተገንብተው ለህ/ሰቡ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ጤና

የዞኑ ህዝብ ጤናው የተጠበቀ ብቁ ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ 1 የገጠርና 1 ሪፈራል ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ 4 የገጠር ሆስፒታሎች ደግሞ ገና በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ በዞኑ 100 የጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችና 402 ጤና ኬላዎች ተገንብተው አገልግሎት አየሰጡ ነው፡፡ በሁሉም ቀበሌዎች ሁለት፣ ሁለት የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች ተመድበው በተለይ አርሶ አደሩን በማገልገል ላይ ሲሆኑ እነዚህ 908 በላይ የሚሆኑ የጤና ኤክስቴሽን ባለሙያዎች 366 700 በላይ የሚሆኑ አባወራዎችን አስመርቀዋል፡፡

የእናቶቸን ሞት በመቀነስ የእናቶች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት 80% ደርሷል፡፡ ጤናን ከመጠበቅ አኳያ የንጹህ ውሃ መጠጥ ውሃ በከተማ 86.2% በገጠር ደግሞ 67.2%

መልካም አስተዳደር

መልካም አስተዳደር አንድ የእድገት መገለጫ በመሆኑ ሰላምንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ፖሊስ ህብረተሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከልን /ኮሙኒቲ ፖሊሲንግ / በሁሉም ቀበሌዎች ተግባራዊ በመደረጉ ወንጀልና ወንጀለኝነት ተመናምኗል፡፡ በኤች አይ ኤድስ በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችንና ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ልማት በማስገባት በኩልም ትልቅ አሰተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ሁሉም ቀበሌዎች ማህበራዊ /ቤቶች በመቋቋማቸውና ስራ አስኪያጆች በመመደባቸው የወረዳው /ቤቶች ጎጥ ድረስ የዞን ከፍተኛ ቤት ደግሞ ወረዳ ላይ በመውረድ ተዘዋዋሪ ችሎት በማስቻላቸው እንዲሁም ከፍተኛው ከቴሌ ኮንፈረንስ ወረዳዎች ላይ ብይን እየተሰጠ በመሆኑ አርሶ አደሩ ያጠፋው የነበረውን ገንዘብ ጉልበትና ጊዜ አስቀርቶለታል፡፡

መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናት በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ከሆነ ወዲህ የነበሩ የተንዛዙ አሰራሮች ተወግደው የደንበኛ ንጉስነት እየተረጋገጠ መጥቷል፡፡

የመስህብ ሀብቶች

በዞኑ በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የመህስብ ሀብቶች የሚገኙ ሲሆን የአፍሪካ የውሃ ማማ እየተባለ የሚጠራው ጮቄና አባሚኒዮስ ተራራዎች፣ ባህረ ጊወርጊስ ሀይቅ፣ ዲማ ቅዱስ ጊወርጊስ ገዳም፣ ሰባራ ድልድይ ድልድይ፣ ህዳሴ ድልድይይ፣ የጫካ ከብቶች፣ መርጡ - ለማሪያም ገዳም፣ 44 የተለያየ ቀለማት ያላቸው ፀበሎች፣ ሙሽሪትና ሙሽራው ድንጋይ፤የእግዜር ድልድይ፣ አባይ ሸለቆ፣ ደብረወርቅ ገዳም፣ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

መሰረተ ልማት

በዞኑ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች 24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ 34 በላይ የሚሆኑ የገጠር ቀበሌዎችም የአገልግሎቱ ተቋዳሽ ናቸው፡፡በስልክ በኩልም 422 በላይ ሽቦ አልባና 11 አከባቢ መደበኛ ስልኮች አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን የዞኑ ሁሉም አከባቢዎች የሞባይል ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

ዞኑ ከሁሉም ወረዳዎች፣ ወረዳን ከወረዳ እንዲሁም ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኙ የክረምትና የበጋ የጠጠርና የጥርጊያ መንግዶች በመንግስትና በህ/ሰቡ ድጋፍ በመሰረታቸው በዞኑ የትራንስፖርቱ አገልግልግቱ በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በበኢፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ/ ICT /በኩል

ምስራቅ ጎጃም በቴክኖሎጅው ዘርፍ ከዞን አስከ ወረዳ፣ ከወረዳ አስከ ቀበሌ ድረስ ቴክኖሎጅን ተደራሽ ለማድረግ ቴክኖሎጅውን በማዳረስ ላይ ነው ፡፡

ስለሆነም ዞኑ 17 ወረዳዎች 3 ከተማ አስተዳደሮች የወረዳ ኔት፣ 39 ስኩል ኔት፣ 381 የቀበሌ ሽቦ አልባ ስልክ ተጠቃሚ ነው፡፡

 
There are no translations available.

አማርኛ

 

Footer

Rightalign

Center

Header

Main Menu


Vister Counter

Content View Hits : 30226

Search

Online Uesr

We have 1 guest online

Archive Content